መዝሙር 45 የሱስ ለዓለም ሲል ሞቶአል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ ለዓለም ሲል ሞቶአል
አምላኬ ሆይ፥ ስጠኝ ማስተዋል።
ጌታ በመስቀል ሞተ ለኔ፤
እንዲያድነኝ ከኩነኔ።
፪፡ እንዴት ይገርማል ታላቅ ፍቅሩ
ማንም አይወደኝ እንደ እርሱ።
እርሱ ካዳነኝ በመሞቱ፥
ሕይወቴን ልስጠው ለክብረቱ።
፫፡ አምላኬ ሆይ ልጅህ አድርገኝ
ከሰይጣን ወጥመድ ሁሉ ፍታኝ።
አንተን ልከተል አስተምረኝ
ላንተም ልሆን በፍቅርህ እርዳኝ።
