መዝሙር 449 ኢየሱስ ሆይ የሞቀ ፍቅርን ስጠኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኢየሱስ ሆይ የሞቀ ፍቅርን ስጠኝ
ፈቃድህን ለመፈጸም አብቃኝ።
ለወንጌል ሥራ ትጉ አድርገኝ፥
መንፈስህ ይምራኝ።
፪፡ በታማኝነት በቅድስናም
እንዳገለግል ኃይልህን ስጠኝ።
በትዕግሥት መከራን እንድቀበል እርዳኝ፥
አቤቱ አጽናኝ።
፫፡ ባለም ለክብርህ እንድኖር እርዳኝ
ጽኑ የሆነ እምነትን ስጠኝ።
ሰላም ዕረፍትን በሰማይ አድለኝ፥
ጉዞዬን ስፈጽም።