Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 448 የጸድቅ ፀሐይ አሁን ወጣ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 448 የጸድቅ ፀሐይ አሁን ወጣ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የጸድቅ ፀሐይ አሁን ወጣ
ብርሃኑ ድል ይነሣል።
ሕዝቦቹ ወንጌልን ሲሰሙ፥
የሱስን ያመልካሉ።
፪፡ የአምላካቸን ግርማ
በምድራችን ላይ በራ፤
ሌሊት አልፎ ቀን ሲተካ
እናመስግን በደስታ።
፫፡ እግዚአብሔር ያጸናል
በሰጠን የተስፋ ቃል፤
ምሕረቱንም ይሰጠናል፥
ሁልጊዜ ይረዳናል።
፬፡ ክርስቶስ ቶሎ ይመለሳል
ሕዝቡን ይሰበስባል፤
አሕዛብንም ይጠራል፥
ከብፅዕናው ይሰጣል።
፭፡ ቆነጃጅት ይወጣሉ
ንጉሡን ሊቀበሉ፤
ለጌታ ይዘምራሉ፥
ምስጋም ያቀርባሉ።
፮፡ እናንተ ሕዝቦች ተመልከቱ
ያምላክ ልጆች ሲመጡ
ፍጹም ነጭ የሐር ልብስ ለብሰው
ወደ ሰርጉ ሲገቡ።
፯፡ ባለም ይታወጅ ወንጌሉ
ይድረስ ለሰዎች ሁሉ፤
ፍቅሩን ስለ ገለጠልን፥
ለዘላለም ይመስገን።

Exit mobile version