መዝሙር 441 እንደ መልአክ የሰማይ ድምፅ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እንደ መልአክ የሰማይ ድምፅ
ድንቅ መልእክቱ ተሰማ፤
ተስፋ በመላው መግባባት
መጽናናት አስተጋባ።
ታገሥ ጨለማው እስኪያልፍ ድረስ፥
ቆይ ወጀቡ ጸጥ እስኪል።
በተስፋ ጠብቅ ይነጋል፥
ጨለማው ይወገዳል።
የተስፋ ድምፅ እንዴት ደስ ያሰኛል
ኀዘኔን በደስታ ይለወጣል።
፪፡ ዓይን ሲይዝ ቀን ድንግዝግዝ ሲል
ጨለማው ሲያጥለቀልቅ።
ድቅድቅ ያለውን ሌሊት ሠርጾ፥
ብርሃን አይታይም ወይ?
ጊዜው በኛ ላይ ሲጨልም፥
ለምን ተስፋ እንቆርጣለን?
እንደምንም ሌሊት ያልፋል፥
እመን ንጋት ይሆናል።
የተስፋ ድምፅ . . .።
፫፡ እንደ መልህቅ ጽኑ ተስፋ
ጨለማውን ያስወግዳል።
ከጌታ ጋር አገናኝቶ፥
መቃብርን ያበራል።
የጨለመውን ልቤን አብራ፥
የደስታ ፍሬን አብዛ።
ቡሩክ የጌታዬ ተስፋ፥
በልቤ ተንሰራፋ።
የተስፋ ድምፅ . . .።
