Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 439 ለዚህ ዓለም ባእድ ሆነን የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 439 ለዚህ ዓለም ባእድ ሆነን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ለዚህ ዓለም ባዕድ ሆነን
የሱስን እንጠብቃለን።
እዚህ ነዋሪ ቤት የለንም፥
ርስታችን በሰማይ ቤት ነው።
ቤታችን ፈራሽ ድንኳን ነው፥
እስክንሄድ ከዚህ ዓለም፥
የሱስ ይመጣል ከሰማይ፥
ሊያወርሰን ርስታችንን።
፪፡ በመከራ በስደትም
አንመረር አናጉረምረም።
ላጭር ጊዜ እንቆያለን፥
የሱስ መጥቶ እስኪወስደን።
ቤታችን . . .።
፫፡ ባዲሲቷ የሩሳሌም
እንግዶች በማንሆንበት።
ከጌታ ጋር ባለ እርስቶች፥
እንሆናለን ያምላክ ልጆች።
ቤታችን . . .።
፬፡ የባዕድን አገር ለቀው
እንደወጡ ስደተኞች።
እንገስግስ እኛም ወደፊት፥
ወደ ሰማይ የተስፋ ርስት።
ቤታችን . . .።

Exit mobile version