መዝሙር 436 ያለም ድካሜና ፈተና ሲያልፍ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ያለም ድካሜና ፈተና ሲያልፍ
ወደ መልካሚቱ ወደብ ስደርስ፥
ሰላም ሳገኝ በጌታዬ አጠገብ፥
ለዘላለም ክብሩን ስጐናጸፍ።
እንዴት ያለ ክብር ይሆናል፥
ክብር ክብር ክብር ለኔ፥
አንድ ቀን በጸጋው፥
ፊቱን ላየው ነው፥
ከርሱ ጋር ስሆን ለኔ ክብሬ ነው።
፪፡ ወሰን የሌለው ጸጋውን ስቀበል
ዘላለማዊ ርስቴ ሲሰጠኝ።
እዚያ ተገኝቼ ፊቱን ሳየው፥
ለዘላለም ክብሩን ስጐናጸፍ።
እንዴት . . .።
፫፡ ወዳጆቼ እዚያ ሊቆዩኝ ነው
የደስታ ምንጭ ዙሪያዬ ሊፈልቅ ነው።
የጌታ ፊት በግልጽ ሊታየኝ ነው፥
ለዘላለም ክብር ልጐናጸፍ ነው።
እንዴት . . .።
