መዝሙር 435 ፊት ለፊት ከክርስቶስ ጋር የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ፊት ለፊት ከክርስቶስ ጋ-ር
ፊት ለፊት እንዴት ይሆን?
በደስታ ባየሁት ጊዜ፥
የሱስ የሞተልኝን?
ፊት ለፊትም አየዋለሁ፥
በሰማየ ሰማያት።
በክብር እከበባለሁ፥
ፊት ለፊት አየዋለሁ።
፪፡ አሁን በድካም እያለሁ
ጨለማው ሲጋርደኝ።
ግን ክብሩ የሚታይበት፥
የብርሃን ቀን ይመጣል።
ፊት ለፊትም . . .።
፫፡ እንዴት ደስ ይለኝ ፊቱን ሳይ
ኀዘን ሕመም አልፎ ሳይ።
ጠማማው መንገድ ሲቀና፥
ጨለማውም ሲበራ።
ፊት ለፊትም . . .።
፬፡ ፊት ለፊት ወይ መታደሌ
ፊት ለፊት ሳውቅና ሳይ።
ፊት ለፊት ከመድኃኒቴ፥
ከአፈቀረኝ ኢየሱስ ጋር።
ፊት ለፊትም . . .።
