መዝሙር 43 መድኃኒታችን ሲሞት ስለኛ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ መድኃኒታችን ሲሞት ስለኛ፥
ዕዳ ተከፍሎ ድልም ተገኘ።
ከኦሪት መርገም ከኃጢአት፥
ክርስቶስ ገዛን ሁላችንን።
ሰው ሆይ ስማ፥ እመን የምሥራችን፤
ክርስቶስ ሲሞት ተገዛን ሁላችን።
ደሙ በመስቀል ከፈሰሰ፥
ዕዳችን ተደመሰሰ።
፪፡ አርነት ወጣን ፍርድ የለብንም፤
ሕሊናችንም አይወቅሰንም።
የሱስ ወደኔ ኑ ይለናል፥
ሰምቶ የመጣ ይድናል።
ሰው ሆይ . . .።
፫፡ እንዴት ታላቅ ነው የአምላክ ጸጋ!
ልጆቹ ሆንን የራሱ መንጋ።
ፍቅሩ ይገርማል ያምላካችን፤
ክርስቶስ ገዛን ሁላችንን።
ሰው ሆይ . . .።
