መዝሙር 429 እኔ መናኝ መንገደኛ ነኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እኔ መናኝ መንገደኛ ነኝ
ለጥቂት ጊዜ ብቻ በዚህ ልኑር።
ከአምላክ ሕዝብ ጋር እጓዛለሁኝ፥
ጌታን ተከትዬ እሄዳለሁ።
ወደዚያም አቸኩላለሁ፥
ለጥቂት ጊዜ ብቻ በዚህ ልኑር።
፪፡ ፋሲካዬን ልብላ በፍጥነት
ቅዱስ ደሙ የልቤን መድረክ ይንካ።
ወዳገሬ ልሂድ ከባርነት፥
ከሰይጣን ሥልጣን ልውጣ አርነት።
አምላክ ይጠራኛል ለሕይወት፥
በቅዱስ በንጹሕ ደሙ ገዝቶኛል።
፫፡ ወደ ከነዓን ዓይኔ ያያል
ለዘላለም ለዘላለም ብሩህ ነው።
በዚህ በጨለማ ሞት ያስፈራል፥
ድካሜ ሁልጊዜ ይጥለኛል።
ወደ አገሬ ዓይኔ ያያል
ለዘላለም ለዘላለም ብሩህ ነው።
፬፡ በዚች ምድር ዕረፍት አይገኝም
ወዲያ ነው ወዲያ ነው ምኞቴ።
በዚያ ሞት ከቶ አያስፈራኝም፥
ድካም አይሰማኝም ጠላት የለኝም።
ኃጢአት አያስጨንቀኝም፥
ወዲያ ነው ወዲያ ነው ምኞቴ።
፭፡ ቸር እረኛዬ አትተወኝ
ከኔ ጋራ ከኔ ጋራ ዘወትር ሁን።
ወደ ብፅዕና እስክታደርሰኝ፥
ለዓይኔ እስክትገለጥልኝ።
ቸር እረኛዬ አትተወኝ፥
ከኔ ጋራ ከኔ ጋራ ዘወትር ሁን።