መዝሙር 426 ስንሰበሰብ በኤደን አንድ ቀን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ስንሰበሰብ በዔድን አንድ ቀን
ከዚህ ምድር ሥቃይ ስንድን።
የዘንባባ ዝንጣፊዎች ይዘን፥
እንቅረብ ወደ አምላክ ዙፋን።
ወደ ላይ ስንደርስ፥
ወደ ላይ ስንደርስ።
የዘላለም ብፅዕና ይቈየናል፥
ወደ ዔድን አንድ ቀን ስንደርስ።
፪፡ ስንደርስ ወደ ዔድን አንድ ቀን
ጻድቃን ሁሉ ይቀበሉናል።
የሰማዕታት ጭፍራም ደስታችንን፥
ከእኛ ጋር ይካፈለዋል።
ወደ ላይ . . .።
፫፡ የሱስም ወዲያ አድርሶን
እርሱ ራሱ ይቀበለናል።
የሙሽራም ልብሳችንን አልብሶን፥
ከርሱ ጋር ያስቀምጠናል።
ወደ ላይ . . .።
