Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 425 ስንጓዝ በደረቅ አገር የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 425 ስንጓዝ በደረቅ አገር የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ስንጓዝ በደረቅ አገር
ከዚህ ከሚጠፋ ዓለም፤
በዝማሬ እንሻገር፥
ወደ አዲስ የሩሳሌም።
እንደ ባሕር ሞገድ ጩኸት፥
በሰማያት መዝሙሩ ይደምቃል፤
ኃይል ምስጋና ክብር ስግደት፥
ላምላክ በግ ይገባዋል።
፪፡ በምድር ለስደተኞች
ኀዘን መከራ ይበዛል፤
ግን ለጽዮን መንገደኞች፥
አክሊል ተዘጋጅቶአል።
እንደ ባሕር . . .።
፫፡ እስራኤል በባቤል ወንዞች
እያለቀሱ ሲኖሩ፤
የየሩሳሌምን ደጆች፥
ሁልጊዜ አስታወሱ።
እንደ ባሕር . . .።
፬፡ የሰማይ ወራሾች ሁሉ
በምድር እንዳትቀሩ፤
ባምላክ ኃይል በቅዱስ ቃሉ፥
በየቀኑ ተመሩ።
እንደ ባሕር . . .።

Exit mobile version