Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 42 መስቀልህን ተሸክመህ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 42 መስቀልህን ተሸክመህ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ መስቀልህን ተሸክመህ
ወደ ሞት ሄድህ ጌታ
ኃጢአተኞችን ለማዳን
ተሠዋህ በጎልጎታ።
ግሩም ፍቅርህ
ቅዱስ ደምህ
ለእኛ ነው የተሰጠ።
፪፡ የመስቀል ሸክም ከባድ ነው
ሲጨመር የኛ ዕዳ
ጌታ የሱስ እንዴት ቻልኸው
መራራውን የሞት ጽዋ?
አሳስበን
ድንቅ ፍቅርህን
ነፍስን የሚያረካ።
፫፡ የመስቀልን ሞት መረጥህ
ያባትህን ዙፋን ትተህ
ፍቅርህን ልትገልጥልን
ስለኛ ተዋረድህ።
ይታገሣል
ያሸንፋል
ጌታ ሆይ፥ ያንተ ፍቅር።
፬፡ በመስቀል ሥቃይ ጌታ
ሞትን አሸነፍህልን።
ድልን ሰጥተኸን በደስታ
ወደ ሰማይ አድርሰን።
በሃይማኖት
የነፍስ ዕርፍት
በዚያ እናገኛለን።

Exit mobile version