መዝሙር 418 ነገ በሚሆነው ከቶ አላሰብም የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ነገ በሚሆነው ከቶ አላሰብም
ሀዘን ቢሆን ወይም ደስታ።
ጌታዬ ሁሉን ነገር ያውቃልና፥
የኔ መጨነቅ ከንቱ ነው።
በእምነት ልኑር ከየሱስ ጋራ
ተማምኜ በታላቅ ፍቅሩ።
ተጠልዬ በፍቅር ክንፉ ሥር፥
በእምነት ልኑር ምንም ሳልፈራ።
፪፡ በሕይወቴ ውስጥ ማዕበል ተነሥቶ
መንገዴን ቢያጨልምብኝ፥
በሚያስፈራ ነገር አልደነግጥም
ጌታ ይመራኛልና።
በእምነት ልኑር . . .።
፫፡ አውቃለሁኝ በደንብ እንደሚመራኝ
በምንም ዓይነት ችግር ውስጥ።
ለምንስ እኔ እጨነቃለሁኝ፥
የሱስ ከኔ ጋር ከሆነ።
በእምነት ልኑር . . .።
፬፡ ጌታችን ወዳለም አንድ ቀን ይመጣል
ችግራችን ሁሉ ያልፋል።
ከርሱም ጋር በደስታ እንሄዳለን፥
ወደ ላይኛው ቤታችን።
በእምነት ልኑር . . .።
