መዝሙር 416 በእግዚአብሔር የሚታመኑ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ በእግዚአብሔር የሚታመኑ
አዲስ ኃይል ይቀበላሉ።
ይሮጣሉ አይታክቱም
ይሄዳሉ አይደክሙም።
በእግዚአብሔር የሚታመኑ፥
አዲስ ኃይሉ ይቀበላሉ።
እርሱን የሚጠባበቁ፥
ጽናት ያገኛሉ።
፪፡ በእምነት የሚጠባበቁ
በመንፈስ ይበረታሉ።
ቀን በቀን ይታደሳሉ፥
ፍሬን ያፈራሉ።
በእግዚአብሔር . . .።
፫፡ ለደከሙ ኃይልን ይሰጣል
ብርታትንም ይጨምራል።
በልጁ ደም ስለዋጀን፥
ዘላለም ይመስገን።
በእግዚአብሔር . . .።
