መዝሙር 409 የሱስን ትቼ ዓለምን ባተርፍ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስን ትቼ ዓለምን ባተርፍ
የዕለት ሕይወቴ ጥቅመ ቢስ ነው።
በሀብቴ ብዛት እረፍት የለኝም፥
ልቤም ሰላምን አያገኝም።
የሱስን ትቼ ዓለምን ባተርፍ፥
ጥረቴ ሁሉ አይረባኝም።
ይልቅ ኢየሱስን የኔ ባደርገው፥
ለልቤ ሰላም አገኛለሁ።
፪፡ ሰዎች ቢያፈቅሩኝ ሀብቴም ቢበዛ
ስሜንም ደግሞ ቢያከብሩልኝ፤
ተስፋ ባይኖረኝ ልሠራ ወደብ፥
ተጕዤ ሄጄ የት ላርፍ ነኝ።
ኢየሱስን ብክድ የሞተለኝን፥
መስቀሉን ብጥል ያዝ ያለኝን፥
ጌታ ሲገለጽ በዕለተ ምጽአት፥
ማንም አይችልም እኔን ሊያድን።
፫፡ አልችልም እኔ ልኖር ብቻዬን
ያለ ኢየሱስ በዚች ዓለም።
መንገዴ ያለ እርሱ ይጨልማል፥
ልቤም በኃዘን ይጨነቃል።
ብኖርስ እንኳ ያለ መድኅኔ፥
በጠራኝ ጊዜ ምን ይዋጠኝ፥
በሌላ መንገድ ልሄድ ብሞክር፥
ሕይወት የለኝም ለዘላለም።
፬፡ የየሱስ መሆን ታላቅ ደስታ ነው
ልብ የሚፈውስ ቸር አዳኝ ነው።
ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ይለኛል፥
ልቤን በደሙ ያጥብልኛል።
የሱስን ብይዝ የሱስን ብቻ፥
ምንም ባልፈልግ ከርሱ ሌላ።
የሚያስፈልገኝን ይሰጠኛል፥
ለዘላለም ይጠብቀኛል።