መዝሙር 407 ወደ ፊት ሂድ ገስግሥ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ወደ ፊት ሂድ ገስግሥ በጌታ ታመን
የሰጠውን ተስፋ ሁሉ አስታውስ።
በቀና መንገዱ እርሱ ይመራል፥
መስክረው አምነው ለሚታዘዙ ሁሉ።
እመነው ታዘዝ እመነው ታዘዝ፥
ጌታ ይጠራሃል ጊዜ አታባክን።
የምሕረቱ ብርሃን ደምቆ ያበራል፥
ለጌታ መስክር እመነው ታዘዘው።
፪፡ ወደ ፊት ገስግሥ እንድታገኝ ጽናት
በጌታ የሚያምኑ አላቸው ዕረፍት።
የደኅነንት ስጦታ ተስጥቶአል፥
መስክረው አምነው ለሚታዘዙ ሁሉ።
እመነው ታዘዝ . . .።
፫፡ ወደ ፊት ሂድ ገስግሥ ኃይልህን አድስ
ዋጋህን ተቀበል አክሊል ተቀዳጅ።
ፍቅሩ ወሰን የለው ችሮታው ብዙ፥
መስክረው አምነው ለሚታዘዙ ሁሉ።
እመነው ታዘዝ . . .።
