መዝሙር 406 የአምላክ ጸጋ ምስጢር ነው የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የአምላክ ጸጋ ምስጢር ነው
የገለጠው ለኔ፤
የየሱስ ክርስቶስ ፍቅርም፥
ለርሱ የዋጀኝን።
ግን አውቃለሁ የአመንኩትን፥
ተረድቻለሁ ችሎታ እንዳለው፤
ከኃጢአት እንዲጠብቀኝ፥
እስከሚመጣበት ቀን።
፪፡ ጌታ እንዴት እንደ ሰጠኝ
አዳኙን ሃይማኖት፤
እንዴትም እንዳጸደቀኝ፣
ልረዳው ባልችልም።
ግን አውቃለሁ . . .።
፫፡ አላውቅም መንፈሱ እንዴት
በሰው እንዲሠራ፤
እየገለጠ የሱስን፥
እየሰጠ እምነትን።
ግን አውቃለሁ . . .።
፬፡ የጌታን መምጫ አላውቅም
ጥዋት ቢሆን ማታ፤
እንዴት እንድሄድ አላውቅም፥
በግር ቢሆን ባየር።
ግን አውቃለሁ . . .።
