Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 404 ጌታ የሱስ ከኔ ጋር ነው ወይ? የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 404 ጌታ የሱስ ከኔ ጋር ነው ወይ? የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ጌታ የሱስ ከኔ ጋር ነው ወይ?
ልቤ ሰላምን ሲያጣ፥
ሸክሜ ሲከብድ ጭንቀት ሲበዛ፥
መንገዴም አድካሚ ሲሆን።
አዎን ይረዳል አዎን ይረዳል
በኀዘኔም ያዝናል
ቀኑ አድካሚ ሌሊቱም ከባድ ሲሆን
ይረዳኛል።
፪፡ ጌታ የሱስ ከኔ ጋር ነው ወይ?
ጨለማ ሲከበኝ
ብርሃን ሲጠፋ ሌሊት ሲቃረብ
በውነት ረዳቴ ነው ወይ
አዎን ይረዳል . . .።
፫፡ ጌታ የሱስ ከኔ ጋር ነው ወይ?
በፈተና ስጠመድ
ለከባድ ጭንቄ መድኃኒት ሳጣ
ሌሊቱን እንባዬን ሳፈስ።
አዎን ይረዳል . . .።
፬፡ ጌታ የሱስ ከኔ ጋር ነው ወይ?
ወዳጆቼ ሲለዩኝ
ልቤ በከባድ ኃዘን ሲሞላ
የሱስ ይመለከታል ወይ?
አዎን ይረዳል . . .።

Exit mobile version