Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 403 ስንጓዝ ሳለህ በጠባቡ መንገድ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 403 ስንጓዝ ሳለህ በጠባቡ መንገድ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ስትጓዝ ሳለህ በጠባቡ መንገድ
የኃጢአት ሸክም ይከብድሃል ወይ?
ለየሱስ ስጠው ሁሉን ተናዘዝ፥
በጠባቡ መንገድ ይባርክሃል።
በጠባቡ መንገድ ከየሱስ ጋር ሂድ
ሸክምህን ሁሉ ይሸክመዋል፤
ኀዘንህን ሁሉ ይካፈለዋል፥
ጭንቀትህን ሁሉ ያርቅልሃል።
፪፡ ስትፈተን ሳለህ ተስፋ ስትቆርጥ
የሱስ ይረዳሃል ያበረታሃል፤
የልብህን ጥማት የሱስ ያረካል፥
ከሕይወት ምንጭ ውኃ የሱስ ያጠጣሃል።
በጠባቡ መንገድ . . .።

Exit mobile version