Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 400 ደስ ይበለኝ ኀዘን ይራቅልኝ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 400 ደስ ይበለኝ ኀዘን ይራቅልኝ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ደስ ይበለኝ ኀዘን ይራቅልኝ
እግዚአብሔር ይወደኛል።
አምላካችን አባት ከሆነልኝ፥
ስለ ልጁ እርሱ ያስባል።
በየደቂቃው የሚደርሰኝን፥
አባቴ በፍቅሩ ልኮታል።
ለየቀኑም የሚጠቅመኝን
ደስታም ኀዘንም ያካፍላል።
፪፡ ጩኸቴን ለመስማት አይሰለችም
ሸክሜንም ያነሣልኛል።
በድካሜ ከኔ ዘንድ አይለይም፥
ስሙም መካር ኃያል ይባላል።
ክቡር ገንዘቡ እንዳይጠፋበት፥
እርሱ ራሱ ይጠነቀቃል፤
እንደ ቀኑም ኃይሉ ሊሆንለት፥
ልጁን ጸጋው ያበረታዋል።
፫፡ አምላኬ እንዲህ ስታስብልኝ
እኔም ሐሳቤን ልተው እርዳኝ።
እምነትን ከቃልህ ጨምርልኝ፥
በዚህም ወዳገሬ ምራኝ።
ደስ ሲለኝ ስጨነቅም በኀዘን፥
አንተ ሁሉን እንደ ሰጠኸኝ፤
ተስፋህን ተቀብዬ ለማመን፣
ጌታ ሆይ፥ አንተ አስተምረኝ።

Exit mobile version