መዝሙር 397 ያች ታናሽ መንጋ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ያች ታናሽ መንጋ
ብፅእት ናት፥
የክርስቶስ ቤተ ሰብ።
ጠላትም ሲያስጨንቃት፥
እረኛው ታላቅ ነው።
ከመከራ ያድናታል፥
በቃሉም ያበረታታል።
በክንዱ ይሸከማታል፥
ቤቱም ያደርሳታል።
፪፡ በጎቹንም ያውቃቸዋል
እነርሱም ያውቁታል፥
ልባቸው አዲስ ሆኖአል፥
ቃሉንም ያምኑታል።
በመንፈስ ኃይልና ብርሃን፥
ከፍርድ ከሰይጣንም ሥልጣን፥
ተቀበሉ ሙሉ መዳን፥
የአምላክ ቅዱሳን።
፫፡ አቤቱ ልቤን መርምረው
ላንተ ይቻልሃል፥
በፍጹም ያንተ አድርገው፥
ስለርሱ ሙተሃል።
ችሮታህም ሳይታወቀኝ፥
በሕይወትህ የገዛኸኝ፥
እሞት ድረስ ከወደድኸኝ፥
ልወድህ አስተምረኝ።
፬፡ እኔን ትወደኛለህ ወይ
ብለህ አትጠይቀኝ፥
እላለሁ ቸር አምላኬ ሆይ፥
አንተ ታውቃለህ ሁሉን።
ድካም ቢያጒላላኝም፥
በኃጢአት ብጨነቅም፥
ልከተልህ ልወድህም፥
ፈቃዴ ሆኖአል።
፭፡ ስቸር ስፈራ ምላሼን
መስጠት ቢቸግረኝ፥
አንተም ትላለህ ገንዘቤን፥
መውደድ አይገደኝም።
በሞት በሕይወት ወደድኸኝ፥
ላንተ በደምህ ዋጀኸኝ፥
ቸር ወዳጄ ሆይ ላንተ ነኝ፥
በፊት ለወደድኸኝ።
