Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 389 ልባችሁ አይደንግጥ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 389 ልባችሁ አይደንግጥ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ልባችሁ አይደንግጥ
እኔንም እመኑ
ቦታ ሞልቶላችኋል
አብን ብትለምኑ።
ግን ብዙ ቦታ ባይኖር
በላይኛው አገር
እሠራላችሁ ዘንድ
ልሂድ ባላልሁ ነበር።
፪፡ እሰጣችኋላሁ
ሰላሜን በብዙ
በደሜ ታጥባችሁ
ጽድቅን እንድትለብሱ።
ናፍቃችሁ እንደሆን
ወደ አብ ለመሄድ
ለሁሉም እኔ ነኝ
ቀጥተኛው መንገድ።
፫፡ የወይኑ ግንድ እኔ ነኝ
አብ ነው የተከለኝ።
አምኖ የሚጠጣኝ
ፍርድ አያገኘውም።
አምኖ የማይጠጣኝ ግን
ይፈረድበታልም
ላሳልፍ ዓለምን
በምመጣበት ቀን።
፬፡ በጎቼን አውቃለሁ
እነርሱም ያውቁኛል
ድምፄን እየሰሙ
ይከታተሉኛል።
ወደ በጎች ስፍራ
የማይገባ በደጅ
ጻድቅ ሰው አይደለም
ወንበዴ ነው እንጂ።
፭፡ በኔ የሚገባ ግን
በቀጥተኛው በር
ሕይወትን ይወርሳል
በላይኛው አገር።
ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ
ቅጥረኛ ያይደለሁ
ለበጎቼ ቤዛ
ራሴን የለወጥሁ።

Exit mobile version