Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 388 አምላኬ ለኔ ቸር እረኛዬ ነው የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 388 አምላኬ ለኔ ቸር እረኛዬ ነው የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አምላኬ ለኔ ቸር እረኛዬ ነው
ታማኝ ወዳጅ የለኝም እንደርሱ።
እጄን ይዞ መንገዱን ያሳየኛል
ከመከራም ጉድጓድ ያወጣኛል።
እጄን ይዞ መንገዱን ያሳየኛል
ከመከራም ጉድጓድ ያወጣኛል።
፪፡ ያለም ሀብቶች ከንቱ ናቸው ያለርሱ
ዛሬ ታይተው ነገ ይጠፋሉ።
አምላኬ ግን ለዘላለም ይኖራል
ልቤንም መቅደሱ ያደርገዋል።
አምላኬ ግን ለዘላለም ይኖራል
ልቤንም መቅደሱ ያደርገዋል።
፫፡ እኔም ካምላኬ ጋር እራመዳለሁ
ለዘላለም ልጁ እሆናለሁ።
እጄን ይዞ መንገዱን ያሳየኛል
ወደ ሰማይ ቤቴ ያገባኛል።
እጄን ይዞ መንገዱን ያሳየኛል
ወደ ሰማይ ቤቴ ያገባኛል።

Exit mobile version