መዝሙር 387 ምንም ቢሆን ተስፋ አትቍረጥ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ምንም ቢሆን ተስፋ አትቍረጥ
አምላክ ይረዳሃል።
በፍቅሩ ጥላ ሥር ብታርፍ፥
አምላክ ይረዳሃል።
አምላክ ይረዳሃል፥
ቀኑን ሁሉ በመንገድህ፥
እርሱ ይረዳሃል፥
አምላክ ይረዳሃል።
፪፡ በዕለት ኑሮህ ልብህ ሲያዝን
አምላክ ይረዳሃል።
ፍርሃት መንገድህን ሲያጥረው፥
አምላክ ይረዳሃል።
አምላክ . . .።
፫፡ የሚያሻህን እንድታገኝ
አምላክ ይረዳሃል።
ብትለምነው አይነሳህም፥
አምላክ ይረዳሃል።
አምላክ . . .።
፬፡ ምንም ዓይነት ችግር ቢሆን
አምላክ ይረዳሃል።
ብርታት ሲያንስህ ተደገፈው፥
አምላክ ይረዳሃል።
አምላክ . . .።