መዝሙር 384 ማን ነው የሚለየኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ማን ነው የሚለየኝ
ካዳኛችን ፍቅር
ኀዘን ነው ጭንቀት ወይም ችግር
ስደት መራቆት ሰይፍና እስራት
ሊለዩኝ አይችሉም ከፍቅሩ።
ብፁዕ ነው እርሱ የሚታገሥ
ፈተናውን ሲያልፍ በመከራ
የሕይወት አክሊል ይወርሳልና
በእምነት ተጋደል የአምላክ ጭፍራ።
፪፡ ሞትም ቢሆን ሕይወት
መላእክት ኃያላን
አላፊውም ቢሆን ወይም መጪ
ከፍታም ዝቅታም ፍጥረታት ሁሉ
ሊለዩኝ አይችሉም ከፍቅሩ።
ብፁዕ ነው . . .።
፫፡ ጳውሎስ ቢወገር እስጢፋኖስ
ያዕቆብ ቢሠዋ ዮሐንስ
ድል ነሥተው ሄዱ
በርሱ መንፈስ
የአምላክ ልጆች እንገሥግሥ።
ብፁዕ ነው . . .።
