መዝሙር 383 ወደ ተራሮች ዓይኔን አነሣለሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ወደ ተራሮች ዓይኔን አነሣለሁ በመቃተት
ረድኤቴ ከወዴት ይመጣልኛል
ከእግዚአብሔር።
ሰማይና ምድርን የፈጠረ
አምላኬ ፈጥኖ ይደርስልኛል።
፪፡ እግርህን ለመናወጥ አይተወውም ይጠብቃል
አምላክህ ፊቱን ካንተ አይመልስም
ይረዳሃል።
ጠባቂህ አይተኛም አያንቀላፋም፥
በቅዱስ ጥበቃው ይከብሃል።
፫፡ ያህዌ እውነተኛ አምላክህ ነው ከለላህ ነው
በቀኝ እጅህ በኩል ይደግፍሃል ያጸናሃል፥
ጸሐዩ በቀን አያቃጥልህም፥
ጨረቃም በሌሊት አይነካህም።
፬፡ ከሚደርስብህ ክፉ ነገር ሁሉ ይጋርድሃል
መግባትህንና መውጣትህንም ይጠብቃል።
የምናምነው አምላክ ከእኛ ጋር ነው፥
ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም።
