መዝሙር 38 እረኞች በድንገት ብርሃን አዩ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እረኞች በድንገት ብርሃን አዩ
የደስታ የምሥራች ቃል ሰሙ።
ጌታ ለኛ ሲል ወደኛ መጥቶአል
መድኃኒታችን ከሰማይ ወርዶአል
እናክብረው።
፪፡ ቶሎ ፍጠኑ ወደ ቤተ ልሔም
ሂዱና ጌታችንንም እዩ።
እልል እያልን ወደርሱ ቀርበን
እናከብራለን ንጉሣችንን
አዎን፥ ይንገሥ።
፫፡ መላእክት ከእረኞች ጋር ሄዱ
ፍጹሙን ታላቅ መድኃኒት ሲሹ።
ለእርሱም እንዘምር ክብሩን እንግለጽ
የንጉሣችን ልደት ነውና
ሃሌሉያ።
