መዝሙር 377 አንድ ወዳጅ በምሄድበት ሁሉ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አንድ ወዳጅ በምሄድበት ሁሉ
ከኔ ጋር ይመላለሳል፤
ላይኔ አይታይም ግን ቅዱስ ቃሉ፥
ወደ ልቤ ይደርሰልኛል።
ያ ወዳጅ ስለኔ ሞቶ ነበር፥
ከመቃብር ግን ተነስቶአል።
እረኛችን ሆኖ በማይነገር፥
ርኅራኄ ለመንጋው ያስባል።
እረኛችን ሆኖ በማይነገር
ርኅራኄ ለመንጋው ያስባል።
፪፡ ሁልጊዜ የሚያስፈልገኝን
ቸር ጌታዬ ያቀርብለኛል።
ልቤንም የሚያቆስለኝን፥
ፈውሶ ረድኤት ይሰጠኛል።
ላጭር ጊዜ እንዲሰወርብኝ፥
እርሱ ራሱ ገልጦ ነግሮኛል።
ግን ተመልሶ ሲገለጥልኝ፥
ደስታና ሰላም ይሆነኛል።
ግን ተመልሶ ሲገለጥልኝ፥
ደስታና ሰላም ይሆነኛል።
፫፡ ድል የነሣ እሙኑ መድኃኒት
ቶማስ ሲጠራጠር አሰበው።
እንዲሰጠውም ቅዱስ መጽናናት፥
ቍስሎቹን አመለከተው።
ቶማስ ጌታን አውቆ አዲስ ተስፋ፥
ሙሉ እምነትም ተቀብሎ።
ጮኸ በማይነገር ቅዱስ ደስታ፥
ጌታዬና አምላኬ ብሎ።
ጮኸ በማይነገር ቅዱስ ደስታ፥
ጌታዬና አምላኬ ብሎ።
፬፡ ለኔ ደግሞ የሱስ ሆይ ራራልኝ
ያንን ደስታ አትከልክለኝ።
አለማመኔም እንዲጠፋልኝ፥
ቍስሎችህን አሳስበኝ።
ቸሩ አምላክ እኔ ምስኪን ልጅህ፥
ተስፋዬ በአንተ ብቻ ነው።
ኦ ጌታዬ አንተንም የማውቅህ፥
ቍስልህን ስታሳየኝ ነው።
ኦ ጌታዬ አንተንም የማውቅህ፥
ቍስልህን ስታሳየኝ ነው።
፭፡ የተወጋው ልብህ ኦ ቸር መድኀን
ያስበኝ በዓለም በረሃ።
በእምነት ልመልከት ቍስልህን፥
በትካዜና በፍሰሐ፥
ና አሳርፈኝ በርኅሩኅ ዕቅፍህ፥
አድርሰኝ ወደ ኢየሩሳሌም።
ድኜም ፊት ለፊት ኦ ጌታ ልይህ
ኦ መድኃኒቴ ኦ አምላኬም።
ድኜም ፊት ለፊት ኦ ጌታ ልይህ
ኦ መድኃኒቴ ኦ አምላኬም።
