መዝሙር 375 ዓይኖቼን ወደ ተራራ አነሣሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ዓይኖቼን ወደ ተራራ አነሣሁ
ወደሚያፈቅረኝ ርኅሩኅ አባቴ፤
እንደ ተስፋው ልመናዬን ይሰማል፥
ረድኤቱም ደግሞ ፈጥኖ ይደርሳል።
፪፡ ሰማይ ምድር ባሕርንም የፈጠረ
ሁሉን የያዘ በታላቅ ፍቅሩ፤
እንደ ፈቃዱ ለለመነ ሁሉ፥
አትረፍርፎ ጸጋውን ይሰጣል።
፫፡ እኔ ኃጢአተኛ በደለኛ ነኝ
እርሱ ይቅር ባይ አባት ነውና፤
በፊቱ ስንበረከክ በንስሐ፥
በደሌን ደምስሶ ይታደገኛል።
