Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 374 የመንፈሴን ጉድለት የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 374 የመንፈሴን ጉድለት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የመንፈሴን ጉድለት
አምላክ ሆይ አስረዳኝ።
ጸጋን እንዳገኝ
ያን ጤናማ ሕይወት።
የመንፈስ ደኅንነት፥
አትውሰድብኝ።
፪፡ ያለም መንገደኛ
እንደ ችግረኛ
ራሱን በመካድ
ወደ ክርስቶስ ጸጋ
በምነት እንዲጠጋ
ነው ያምላክ ፈቃድ።
፫፡ ለመዳንህ ተግተህ
በምግባር ተመክተህ።
ጻድቅ ከመባል
እንዳንድ ምስኪን ሆነህ
ብትድን በየሱስ
ይህ ይሻልሃል።
፬፡ የሱስ ያዳናቸው
ምስኪኖች ቀራጮች
አመሰገኑት።
ፈሪሳውያን ግን
እንደ ዓለም መድኅን
አልተቀበሉትም።
፭፡ ጽድቅን በመፈለግ
ተስፋዬን ከማድረግ
አምላክ አድነኝ።
ነገር ግን የሱስ ሆይ
ጻድቅና ቅዱስ
እንድሆን እርዳኝ።

Exit mobile version