Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 372 እኔ ኢየሱስን ለማየት የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 372 እኔ ኢየሱስን ለማየት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ እኔ ኢየሱስን ለማየት
ከቶ አልተቻለኝም፥
ወይ ድካም የልቤ ዕውረት፥
እርሱን አያሳየኝም።
የሱስ ና ልቤን አብራልኝ፥
ዓይኖቼን ክፈትልኝ።
ቀና መንገድህን አሳየኝ፥
ከጥፋትም አድነኝ።
፪፡ በባርነት የተገዙ
አርነት ወጥተዋል።
በኦሪት ሕግ ለተያዙ፥
ነጻነት ተሰጥቶአል።
የክርስቶስ ደም ለነፍሳቸው፥
ሕይወት ሆነ ፈውስም፤
የሱስ ክርስቶስ ሞተላቸው፥
እርሱ ነው መድኃኒትም።
፫፡ ማን ነው ዛሬ የሚጠራ
ፍቅሩን የሚገልጥ ማን ነው፤
ለሚሞትስ የሚራራ፥
የሚያድንስ ማነው።
የሱስ ነው መድኃኒታችን፥
ስለ እኛ ሞቶአል።
ቅዱስ ስሙን የሚያምን፥
ለዘላለም ይድናል።

Exit mobile version