Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 369 በሕይወት ማዕበል ጐርፍ ስትቀጠቀጥ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 369 በሕይወት ማዕበል ጐርፍ ስትቀጠቀጥ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ በሕይወት ማዕበል ጐርፍ ስትቀጠቀጥ
ሁሉም ጠፍቶብህ ተስፋህም ሲቆረጥ።
ባርኮትህን ቍጠር ዘርዝር በተራ፥
ወዲያው ታስባለህ ያምላክን ሥራ።
ባርኮትህን ዘርዝር በተራ
አይተህ ተገንዘብ የርሱን ሥራ።
ባርኮትህን ዘርዝር በተራ፥
አይተህ ተገንዘበው ያምላክን ሥራ።
፪፡ በከባድ ሸክም ኃይል ተጭነሃል ወይ?
የጥሪውስ መስቀል ከበደብህ ወይ?
ባርኮትህን ቍጠር ጥርጥር ይብረር፥
በዘመንህ ሁሉም በደስታ ዘምር።
ባርኮትህን . . .።
፫፡ ወደ ሌሎችም ሀብት ስትመለከት
አስብ የክርስቶስን ባለጠግነት።
ባርኮትህን ቍጠር አይገዛውም ሀብት፥
ያንተንም ነፍስ ዋጋ በሰማዩ ቤት።
ባርኮትህን . . .።

Exit mobile version