Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 368 ቅዱስ ቃሉን የሚሰሙ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 368 ቅዱስ ቃሉን የሚሰሙ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ቅዱስ ቃሉን የሚሰሙ
ባምላክ የሚታመኑ።
ፈቃዱን የሚፈጽሙ
ለክብሩ የሚኖሩ።
በመንፈሱ የሚመሩ
ብፅዕናን ያገኛሉ
ሰማይን ይወርሳሉ።
፪፡ እምነታቸው ድል ይነሣል
ጠብ ሁከትም ይጠፋል
ፍቅራቸው ደምቆ ይታያል
ለዘላለም ይኖራል።
የተስፋቸውም መሠረት
ጽኑ ነው እንደ ዓለት
በሞት ሆነ በሕይወት።
፫፡ ብሩህ ብርሃን ከአብ ግርማ
ወረደልን ለእኛ።
ግሩም ሰማያዊ ደስታን
አምላክ በፍቅሩ ሰጠን።
በምድር ያለን ሁላችን
እንቀበል ጌታን
ወደ ሰማይ መግቢያችን።

Exit mobile version