Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 365 የሱስ ወደ ቤቱ ይጠራሃል የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 365 የሱስ ወደ ቤቱ ይጠራሃል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ ወደ ቤቱ ይጠራሃል
ይጠራሃል ይጠራሃል፤
ለምን ከፍቅሩ ብርሃን ኮብልለህ፥
ወደ ሩቅ ትሄዳለህ።
ይጠራሃል ይጠራሃል
የሱስ በፍቅሩ ወደ ቤቱ ይጠራሃል
፪፡ የሱስ ደካሞችን ያሳርፋል
ይጠራሃል ይጠራሃል፤
ከነሸክምህ ሂድ ትባረካለህ፥
ከርሱም ጋር ትኖራለህ።
ይጠራሃል ይጠራሃል . . .።
፫፡ የሱስ ይቆይሃል ና ወደርሱ
ይቆይሃል ይቆይሃል፤
ከነኃጢአትህ በግሩ ሥር ውደቅ፥
ና ምንም አትጠብቅ።
ይጠራሃል ይጠራሃል . . .።
፬፡ የሱስ ሲለምንህ አሁን ስማው
አሁን ስማው አሁን ስማው፤
በርሱ የሚያምኑ አላቸው ደስታ፥
ፈጥነህ ሂድ ወደ ጌታ።
ይጠራሃል ይጠራሃል . . .።

Exit mobile version