መዝሙር 364 የአዳኜን መልካም ጥሪ ሰማሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የአዳኜን መልካም ጥሪ ሰማሁ
ተከተለኝ ተከተለኝ ሲለኝ፥
ቃሉ ዘወትር ይሰማኛል
ተከተል ተከተለኝ ሲለኝ።
ላንተ ስል ከባድ መንገድ ተጓዝሁ፥
ላንተም ስል ሕይወቴን ሠዋሁ፥
መራራ ጽዋውንም ጠጣሁ፥
ተከተል ተከተለኝ እኔን።
፪፡ በደልህን ይቅር እላለሁ
ተከተል ተከተለኝ እኔን
ከኃጢአት ነጻ አወጣሃለሁ
ተከተል ተከተለኝ እኔን፥
አባት ሆኜ እመራሃለሁ
በየብስ ባየር በባሕር ላይ፥
ዘላለም ደስ አሰኝሃለሁ
ተከተል ተከተለኝ እኔን።
፫፡ ሸክምህን በእኔ ላይ ጥለህ
ተከተል ተከተለኝ እኔን፥
የከበደህን እሸከማለሁ
ተከተል ተከተለኝ እኔን።
በርታ አትፍራ ተከተለኝ
ተደገፈኝ በኔ እመን፥
እንባህን ሁሉ አብሳለሁ፥
ተከተል ተከተለኝ እኔን።