መዝሙር 348 ሁሉም ተዘጋጅቶአል ኑ ወደ እኔ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሁሉም ተዘጋጅቶአል ኑ ወደ እኔ አሁን
የሚል የምሥራቹን ቃል።
ጌታ ያሰማናል ተግተን እንገሥግስ፥
በከፈተልን በር ለመግባት።
፪፡ አግኝተናልና ጸጋና ምሕረቱን
አሁን ነው ጊዜው የመዳን።
ሳይዘጋብን ደጁ ጸጸት ሳይገባን፥
እንደ አምስቱ ብልሆች ሆነን እንገኝ።
፫፡ ባዘጋጀልን ቤት ከቅዱሳኑ ጋር
በዘላለማዊ ደስታ።
በምስጋና በመዝሙር በዕልልታ፥
ሃሌ ሉያ እንበል ላዳነን ጌታ።