መዝሙር 345 ከኢየሱስ ጋር በመስቀሉ ሥር የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ከኢየሱስ ጋር በመስቀሉ ሥር
ተገናኝ ወንድሜ ሆይ።
ድምፁን ስማ ሸክምህን ጣለው፥
አዲስ ሕይወት ጀምር።
መስቀሉ ሥር ተንበርክከህ፥
መስቀሉ ሥር የሱስን ተገናኝ።
፪፡ መስቀሉ ሥር ይጠብቅሃል
ክብሩን ሊያካፍልህ።
ፍጹም ደስታ ተዘጋጅቶአል፥
በእርሱ ከጸናህ።
መስቀሉ . . .።
፫፡ መስቀሉ ሥር ሁሉን አስረክብ
የሱስን ተቀበል።
አላፊውን ደስታ ትተህ፥
በፍቀሩ ታምነህ ኑር።
መስቀሉ . . .።
