መዝሙር 344 እንዴት ጸጋ ነው የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እንዴት ጸጋ ነው
እንዴት ደስታ ነው
ለዘላለም በኢየሱስ ማረፍ።
እንዴት መባረክና ሰላም ነው
ለዘላለም በክንዱ ማረፍ።
ዕረፍት ዕረፍት
ከፍርሃት ሁሉ ደኅንነት
ዕረፍት ዕረፍት
በኢየሱስ ዕረፍትን ማግኘት።
፪፡ እንዴት ያምረኛል
በርሱ መደገፍ
ለዘላለም በኢየሱስ ማረፍ።
ኢየሱስንም በእምነት ልደገፍ
ለዘላለም በክንዱ እንዳርፍ።
ዕረፍት . . .።
፫፡ ምን ያሰጋኛል?
ምን ያስፈራኛል?
በጌታ በኢየሱስ ክንድ ልረፍ።
እርሱም ለዕረፍት ሲል ይጠራኛል
ለዘላለም በክንዱ እንዳርፍ።
ዕረፍት . . .።
