Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 34 ከሚያንጸባርቅ ሰማይ በታች የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 34 ከሚያንጸባርቅ ሰማይ በታች የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ከሚያንጸባርቅ ሰማይ በታች
መንጋ ተሰማርቶአል
እረኞች ነቅተው በደስታ
ዙሪያውን ሲጠብቁ
ደማቅ ብርሃንም አበራ
ሌሊቱን አስመሰለው ቀን
ምን ይሆን የታያቸው
እንዲህ የሚያስፈራቸው
፪፡ እረኞች እረኞች አትፍሩ
ሲል መልአክ ነገረ
ለናንተ ታላቅ የምሥራች
አምጥቻለሁ ዛሬ
ክርስቶስ መድኅን ተወልዶአል
በበረት ላይ ተኝቶአል
ድሀ ሆኖ ተወለደ የሰማይ
ንጉሥ ሳለ።
፫፡ የሰማይ መላእክት አንድነት
መዝሙር ኑና አድምጡ
በከበሮ በጸናጽል የሚሰማው ሃሌታ
ክብር ለአምላክ በአርያም
በምድርም ይሁን ሰላም
ፍቅር ለሚናፍቅ ሁሉ ሰላሙ
ይኑርለት።
፬፡ እኔም ከሰማይ ሠራዊት ጋር
ለቅዱስ ያምላክ በግ፥
ከእረኞች ጋር አብሬ በልቤ
ልወድሰው፥
ለሕፃኑ እዘምራለሁ
ኃጢአቴን ስለተወልኝ
ክብር ለአምላክ በአርያም
ስብሐትም ሃሌሉያ።

Exit mobile version