መዝሙር 339 አምላክ ቤቱን አዘጋጅቶልናል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አምላክ ቤቱን አዘጋጅቶልናል
ከኃጢአት ወጥመድ ኢየሱስ ፈቶናል።
ከሞት በኋላ ፍርድ የለብንም፥
ሙሉ ይቅርታ አድርጐልናል።
እንጓዝ ወደ ሰማይ፥
በርሱ ኃይል ተደግፈን።
እንገሥግስ ወደ ላይ፥
ወደ መንግሥተ ሰማይ።
፪፡ ክርስቲያን ባምላኩ ብቻ ሲታመን
የሱስ በጸጋው ይጠብቀዋል።
ልጆቹ በጌታ ስንታመን፥
ወደ ተስፋው አገር እንደርሳለን።
እንጓዝ . . .።
፫፡ በእምነት የዛለ ተስፋ የለውም
በየሱስ የታመነ አያፍርም።
በመድኅኑ ፍቅር ጽድቅን ያገኛል፥
የዘላላም ሕይወትን ይወርሳል።
እንጓዝ . . .።
፬፡ የጨለማ ሥልጣን ቢያስፈራም
የሱስን ይዤ ልኑር በሰላም።
በቸርነቱና በምሕረቱ፥
ድልን አግኝቼ ልጁ ሁኛለሁ።
እንጓዝ . . .።
