መዝሙር 338 የሱስ ክርስቶስ ራሱ ሆነ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ ክርስቶስ ራሱ ሆነ
የኔ ወዳጅ፤
ነፍሴንም ከሞት አዳነ
ይህ ቸር ወዳጅ።
ቅን ልቡ በፍቅር ጋለ
እኛን ወንድሞቼ አለ።
ለኛ ሲል ሕይወቱን ሰጠ
ይህ ቸር ወዳጅ።
፪፡ ሳልወድህም ወደኸኛል
ኦ ቸር ወዳጅ
በምሕረት ተዛምደኸኛል
ኦ ግሩም ወዳጅ
ከጥፋት አውጥተኸኛል
ከመሞት አድነኸኛል
ለልጅነት መርጠኸኛል
ኦ ቸር ወዳጅ።
፫፡ ሁልጊዜ ረድኤት እሻለሁ
ከዚህ ወዳጅ
ችግሬን እነግረዋለሁ
ለዚህ ወዳጅ።
አንዳች ነገር ቢጐድልብኝ
ልመናዬን ሲሰማልኝ
ግሩም ነው ሲያስብልኝ
ይህ ቸር ወዳጅ።
፬፡ ይህ ወዳጅ በኀዘን ሁሉ
ያጽናናኛል
እርሱም ኃጢአቴን ሁሉ
ይሰርያል።
እኔም ሁልጊዜ ስበድል
በርኅራኄ ይጠራኛል
በስሕተቴ ሳይበቀል
ይመራኛል።
፭፡ ሐሳቤንም እጥላለሁ
በዚህ ወዳጅ
ሁሉን እጠባበቃለሁ
ከዚህ ወዳጅ።
አሮጌ ሥጋዬን መግደል
ነፍሴን ከጥፋት መከለል
መከራዬንም ለማቅለል
ይቻለዋል።
፮፡ አምላክ የተዛመዳቸው
እንደ ወዳጅ
ለዘላለም ቡሩካን ናቸው
ኦ ቸር ወዳጅ።
ዘመድ ሁሉ ሲተዋቸው
ሀብት ሁሉ ሲጠፋባቸው
የዘላለም ሀብት አላቸው
በዚህ ወዳጅ።