Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 333 ያዲስ ኪዳን በግ ቅዱስ ካህን የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 333 ያዲስ ኪዳን በግ ቅዱስ ካህን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

ያዲስ ኪዳን በግ ቅዱስ ካህን
የጽድቅ ንጉሥ የዓለም መድኅን።
የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ፥
ቅዱስ ካህን አለን በላይ በሰማይ።
፩፡ ከብዶን የነበረው የሕግ ጭነት
ፍጥረትን ሲያስጨንቅ ስለ ኃጢአት።
የሕዝብን ኃጢአት አንዴ ለማስቀረት፥
የሱስ ሕይወቱን ሰጠ በመስቀል ስቅላት።
ያዲስ ኪዳን በግ . . .።
፪፡ የኃጢአት መጋረጃ እኛን የለየን
የሱስ ተረተረው መሥዋዕት ሆኖልን።
ቅድስተ ቅዱሳን የተስፋው ሀገር፥
በርሱ ልንገባ ቻልን ወደ ሕይወት በር።
ያዲስ ኪዳን በግ . . .።
፫፡ የኮርማ ደም መሥዋዕት ለኛ አያስፈልገንም
አንዴ ተረጭተናል በክርስቶስ የሱስ ደም።
ቅዱስ ያዲስ ኪዳን መካከለኛ፥
ነፍሱን ወዶ ሰጠ ሊሞት ስለእኛ።
ያዲስ ኪዳን በግ . . .።

Exit mobile version