መዝሙር 329 ስላለፈው ቀን ጌታዬ ሆይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ስላለፈው ቀን ጌታዬ ሆይ፥
ረዳቴና አምላኬ ሆይ፥ ተመስገን።
ሁሉን ፈጸምክልኝ እንዲጠቅመኝ፥
አበረታኸኝ ጠበቅኸኝም።
ልጆቹን እንደሚንከባከብ አባት፥
አንተ ደግሞ ለእኔ ሆንክልኝ፥
በርኅሩኅ እጆችህ ተሸከምከኝ፥
ልጅህን ችላ አላልከኝም።
፪፡ በዚህ ሌሊትም እረፍትን ስጠኝ
በጽኑ እጆችህ አባቴ ሆይ።
መላክህን ላክ እንዲጠብቀኝ፥
ታማኝ ሆኖ እንዲቆምልኝ።
በዓለም ውስጥ ሰላም አይገኝም፥
የነፍሴ እረፍት አንተ ብቻ ነህ።
ርኅሩኅ አዳኜ ሆይ፥ እኔን ምራኝ፥
በመንግሥትህ ውስጥ ተቀበለኝ።
