መዝሙር 328 ከዕለታት አንድ ቀን አሁን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ከዕለታት አንድ ቀን አሁን
ከእኛ አልፎአል
ፀሐይ ሲጠልቅም ሌሊቱን
አምላክ ልኮልናል።
፪፡ ግን እርሱ አይለዋወጥም
አያልቅም ፍቅሩ፤
ቀናችንም ሌታችንም
ነው እንደ ፈቃዱ።
፫፡ አምላክ ሆይ በእጅህ ልሁን
ጉዳትን አልፈራ፤
ሲነጋም ቅዱስ ስምህን
በምስጋና ልጥራ።
፬፡ ግን በዚህ ሌት የሞት መልአክ
የጠራኝ እንደሆን፥
የአንተ ነኝ ቸር አምላክ ሆይ፤
ከአንተም ዘንድ ልሁን።
