Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 325 የሱስ ሆይ የልቤ ተስፋ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 325 የሱስ ሆይ የልቤ ተስፋ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ ሆይ የልቤ ተስፋ
ና ና ነፍሴን ደስ አሰኝ።
ደግፈኝ በአንተ ጸጋ
በቃልህ ብርሃን ሁነኝ።
ና ወደኔ የሱስ ሆይ
ከኔም ዘንድ ዘወትር ቆይ።
፪፡ በቅዱስ ስምህ ልጀምር
ዕለት ዕለት ሥራዬን።
በረከት በላዬ ጨምር
እስክፈጽም ዕድሜዬን።
ና ወደኔ . . .።
፫፡ ያፌን ቃል የልቤን አሳብ
በምሕረትህ እይልኝ።
ነዋሪ ሀብት ለመሰብሰብ
ሁልጊዜ አነቃቃኝ።
ና ወደኔ . . .።
፬፡ ቀን አልፎ ሌሊት ሲተካ
ጠብቀኝ ቸሩ ጌታ።
አትራቅብኝ ሲነጋ
ኢየሱስ ሁን ከኔ ጋራ።
ና ወደኔ . . .።

Exit mobile version