Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 324 በቃ አልፈልግም የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 324 በቃ አልፈልግም የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ በቃ አልፈልግም ልቤን ውሰደው
አእምሮዬን ግዛው ላንተው አድርገው።
ዝም ልበልና ኃይልህን ልመልከት
ሌላው አሳቤ ይብቃ ይከተት።
አቤት እንዴት ታላቅ ነህ?
እንዴት ታማኝ ነህ?
እንዴት ፍጹም ነህ?
የዘላለም አምላክ የማትለወጥ፥
የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ።
፪፡ ሌት በመኝታ እንዳስብ አንተን
ቀን በሥራዬ እንዳውጠነጥንህ።
ነህና ለነፍሴ እርካታና ደስታ፥
ክብርህን ላስበው ሁሌ ጠዋት ማታ።
አቤት እንዴት . . .።
፫፡ እጄን ባፌ ላይ አድርጌ ተደነቅሁ
ሥራህንም ሳየው በደስታ ተሞላሁ።
በእውነት ተረዳሁ ያንተን ታላቅነት፥
እንዲሁም አስተዋልኩ የኔን ውዳቂነት።
አቤት እንዴት . . .።
፬፡ ላንተ የሚገባህን ክብርህን ለመስጠት
በመንፈስ ሳስብህ ያኔ ተረዳሁት።
አሁን ቃል ኪዳኔ የመጨረሻው፥
ተዋርጄ እንድኖር ነው ላንተ የምሻው።
አቤት እንዴት . . .።

Exit mobile version