መዝሙር 322 እኔ መናኝ መጻተኛ ነኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እኔ መናኝ መጻተኛ ነኝ
በጨለማ ብርድ የዞርሁኝ።
የሱስ እረኛዬ አገኘኝ፥
አሁንም ወደ ላይ እጓዛለሁ።
በውነት ቸርነትህ ምሕረትህ
ይከተሉኛ ሁልጊዜ
ሁልጊዜ በሕይወቴ ሙሉ።
በውነት ቸርነትህ ምሕረትህ
ይከተሉኛ ሁልጊዜ
ሁልጊዜ በሕይወቴ ሙሉ።
፪፡ ሲደክመኝ ነፍሴን ያጽናናታል
በየቀኑ ኃይል ይሰጠኛል።
ጸጥ ባሉ ውኆች ይመራኛል፥
ስጓዝም ይጠብቀኛል።
በውነት ቸርነትህ . . .።
፫፡ በጨለማ ጉዞ ስዋልል
መድኅኔ አብሮኝ ይጓዘል።
ወዳዘጋጀልኝ መኖሪያ፥
በታላቅ እጁ ይመራኛል።
በውነት ቸርነትህ . . .።
በውነት በጌታ ቤትም ለዘላለም
እኖራለሁ፥
የቀረበልኝን እመገባለሁ።
በውነት ቸርነትህ ምሕረትህ
ይከተሉኛል
ሁልጊዜ በሕይወቴ ሙሉ፥
ሁልጊዜ በሕይወቴ ሙሉ።