Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 319 ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 319 ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር
በታላቅ ግርማህ ጠላት ይሸበር፥
ሃሌ ሉያ።
ስምህ ይለምልም ዙፋንህ ይጽና
ለባሪያህ በጎ ውለሃልና፥
ሃሌ ሉያ።
አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው።
አምላክ እረኛዬ ነው፥
አምላኬ እረኛዬ ነው።
፪፡ ውዳሴ ካፌ አንተን ከልቤ
ከቶ አይጠፋም ብኖር ተርቤ፥
ሃሌ ሉያ።
የቅርብ ወዳጄ የጦር አዝማቼ፥
ብቻ አትለየኝ ልቆይ ተግቼ፥
ሃሌ ሉያ።
አምላክ . . .።
፫፡ ብቆም ብቀመጥ ብሄድ ብተኛ
አምላኬ አንተ ነህ የኔ ጓደኛ፥
ሃሌ ሉያ።
ጽልመት ቢመጣ የመከራ ጉም፥
አንተን ጠርቼ እኔ አላፈርኩም፥
ሃሌ ሉያ።
አምላክ . . .።
፬፡ ሕመም ሞትህን ሥጋዬ ለብሶ
ይዋረድ ይለፍ ጽዋህን ቀምሶ፥
ሃሌ ሉያ።
የጻድቁን ሞት ነፍሴ ተጠምታ፥
ትጥገብ አትፈር ስምህን ጠርታ፥
ሃሌ ሉያ።
አምላክ . . .።

Exit mobile version