መዝሙር 318 ደካማ መንገደኛ ነኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ደካማ መንገደኛ ነኝ
አንተ ግን ኃያል አምላክ፥
በጉዞዬ ሁሉ ምራኝ።
በብርቱ እጅህ ያዘኝ፥
ያንን ሰማያዊ ኅብስት፥
መግበኝ እንዳይርበኝ፥
መግበኝ እንዳይርበኝ።
፪፡ ከኃጢአት የሚያነጻኝን
የሕይወትን ምንጭ አፍልቅ።
በእሳት በደመና ዓምድ፥
መንገዴን ሁሉ ምራኝ።
ኃያል አዳኝ ኃያል አዳኝ፥
ጋሻና ብርታት ሁነኝ፥
ጋሻና ብርታት ሁነኝ።
፫፡ ፍርሃትና ጥርጥርን
ፍጹም ከኔ አርቀህ።
አዲሷ ኢየሩሳሌም፥
በሰላምህ አድርሰኝ።
ለዘላለም ለዘላለም፥
እንድወድስህ አብቃኝ፥
እንድወድስህ አብቃኝ።
