መዝሙር 317 እጆቼን ይዘህ ምራኝ መድኃኒቴ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እጆቼን ይዘህ ምራኝ መድኃኒቴ
ከአንተ ጋራ ልጓዝ ወደ ሰማይ።
የብቸኛ ጉዞዬ ያስፈራኛል፥
ከአንተ ጋራ መሆን ያስመኘኛል።
፪፡ በጸጋህ ሙላት ልቤን አጥለቅልቀው
በእግሮችህ ሥር ልረፍ ከችግሬ፥
ቃልህን ልመገበው ደጋግሜ፥
በኀዘን ሆነ ደስታ ነህ ተስፋዬ።
፫፡ የምሄድበት መንገድ ድንግዝግዝ ነው
በአንተ እንዲበራ እማጠናለሁ።
እጆቼን ይዘህ ምራኝ መድኃኒቴ፥
ከአንተ ጋራ ልጓዝ ወደ ሰማይ።
